ስለ ሚርሃቭ

 

‘ሚርሃቭ’ ማህበረሰባዊ ድርጅት ሲሆን የተለያዩ የኢትዮጵያዊያን ድርጅቶች መሪዎችና የለዉጥ አምጪ ግለሰቦች ተነሳሽነት እንዲሁም በእውነተኛ ተሳትፎና ትብብር  ሰፊ ተፅዕኖ ለኢትዮጽያዊያንም ሆነ ለሰፊው የእስራኤል ማህበረሰብ ላይ ማምጣት እንደሚቻል በማመንና በተናጥል ቢሰሩ ሊሳኩ የማይችሉ ግቦችን በጋራ እዉን ማድረግ እንደሚቻል  በማመን የተቛቛመ ደርጅት ነው።

 

የሚርሃቭ ግብ

 

 በእስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን የወደፊት እጣ ፈንታ በተመለከተ  ሃሳቦችን ለማመንጨትና ተፅዕኖ ለማድረግ።

 

የሚርሃቭ አላማ

 

የኢትዮጵያዊያንን ራዕይና ግብን በማህበረሰቡ መሪዎች፣ የለዉጥ ተንቀሳቃሾችና ድርጅቶች መሰረት የተቀናጀ ሰነድ ማዘጋጀ ነው።

ይሄ የጋራ የሚርሃቭ ሰነድ አላማው ለ እስራኤላዊ ኢትዮጵያዊያን በሰፊ ተሳትፎ የወደፊት እጣ ፋንታዉን ማህበረሰቡ እራሱ እንዲወስንና ለሚቀጥሉት አመታት ወዴት አቅጣጫ እርምጃ መውሰድ እንደሚፈልጉ በመወሰን በዚህ ሰነድ እንደ መመሪያ ብርሃን ለመጠቀም ነው።

ሚርሃቭ ስራዉን የጀመረው በ ሜይ 2014 ሲሆን አባላቱንም እንደ ሞያዊ አማካሪዎቹ አድርጎ በመውሰድ ነው።

 

የሂደቱ መጨረሻ ዲሴንበር 2015 ነው ተብሎ ታቅዷል።

 

የሚርሃቭን የሚስጥራዊነት ሰነድ ለማውረድ እዚህ ይጫኑ።